South Gondar Zone ICT

Investment Opportunity

SECTORS

User Login Area

sgzone::Home

የደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር ታሪክ አጭር ዳሰሳ

ከጥንታዊ ዘመን እስከ 6ኛው ክፍለ ዘመን


በጣም ጥንታዊ በሆነው የታሪክ ዘመን በጥንታዊቷ ቤጌምድር ይኖር በነበ ረው ህ/ሰብ የኦሪትም ሆነ የክርስትናን ዕምነቶች ከመከተሉ በፊት ተፈጥሮአዊ የሆኑ አምልኮታዊ ስርዓቶችን ይፈጽምና ይከተ ል እንደነበር በዋሻ እንድርያስ የሚገኙት ተጨባጭ ቁሳዊ መረጃዎች ያረጋግጣሉ።

በዛሬዋ ደቡብ ጎንደር በጥንታዊቷ ቤጌምድር ከ5ኛው ክ.ዘ ዓ.ዓ በፊትና ከዚያ በኋላ እስከ 4ኛው ክ.ዘ ዓ.ም ድረስ ጠንካራ ኦሪታዊ ባህል ተስፋፍቶ እንደነበር በታሪክ የሚታወቅና በጣና ቂርቆስ የሚ ገኙት ቁሳዊ መረጃዎች ያረጋግጣሉ።

የክርስትና ሀይማኖትን ወደ ዞኑ ከመግባቱና ከመስፋፋቱ ጋር በተያያዘ በ4ኛው ክ.ዘ አብርሃ ወአጽ ብሃ ከአቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሀን ጋር በዞኑ በኦ ሪት ዕምነት ምትክ ክርስትናን የሰበኩበትና ያወጁበት ጣ ና ቂርቆስ ይገኛል።እንዲሁም በ6ኛው ክ.ዘ እነ አጼ ገብረመስቀል፤አቡነ አረጋዊ እንዲሁም ቅዱስ ያሬ ድ በዞኑ ተንቀሳ ቅሰው በ4ኛው ክ.ዘ የጀመረውን የክርስትናን ሀይማኖትና ባህላዊ እሴት መሰረቱን እን ዲጥል አስተዋጽኦ አበር ክተዋል።

ከመካከለኛው ዘመን እስከ 17ኛው ክፍለ ዘመን

ከ9ኛው እስከ 12ኛው ክ.ዘ በዞኑ የውቅር አንድ ወጥ ዓለት ፍልፍል ሀይማኖ ታዊ ግብረ ህንጻዎች የተስፋፉበት ዘመን ሲሆን ይህም በፋርጣ፣በላይ እና ታች ጋይንት የዘመኑን ስልጣኔ አሻራዎች እናገኛ ለን።በዞኑ በ13ኛው ክ.ዘ መገባደጃ ላይ ከተከናወኑ ታሪካዊ ክንዋኔዎች ውስጥ በታች ጋይንት ዳቃ ቂር ቆስ በተባ ለው ስፍራ የተፈጸመው ንና የዛግዌ እና ሰለሞናዊ ስርወ መንግስታት የስልጣን ሽግግር ዕል ባት ያገኘበት በታሪካዊ ነቱ ይጠቀሳል።

በ14ኛው ክ.ዘ መጀመሪያዎቹ ላይ በዐጼ ሰይፍ አርእድ የአሁኗ የዞኑ ርዕሰ ከተማ ደብረ-ታቦር የተ ቆረቆረችበት መንፈሳዊ ይዘት ያላቸው የአብያተ ክርስቲያናት ምስረታና ግንባታ ባህል የተጣለበት ነበር።

በ17ኛው ክ.ዘ መጀመሪያዎቹ 3 አስርት አመታት በዐጼ ሱስኑዩስ ዘመነ መ ንግስት በያኔዋ ቤጌም ድር በፋርጣ ወረዳ በአሪንጎ፤በስማዳ ወረዳ በአንፋርጌ፤በምስራቅ እስቴ ወረዳ በብሩ አደጌ የርብ ወንዙ ድልድይ ከሀይማኖታዊ ተቋምነት ወጣ ባለ መልኩ ለወታደራዊና አስተዳደራዊ ዓላማ የተገነቡ የዘመኑ ን የህንጻ ግንባታ ባህልና ስልጣኔ አሻራ ሆነው እናገኛቸዋለን።

በ17ኛው ክ.ዘ 50ዎቹ በኋላም መቀመጫቸውን በጎንደር ያደረጉ ነገስታት በስልጣናቸው ላይ የሚ መጣን ዕክል ለመከላከል የንጉሱ ወንድም ወይም የቅ ርብ ዘመዶች የሚ ጋዙበት በዞናችን የወህኒ ዓምባ ን መስርተው ሲጠቀሙ በት ነበር።

19ኛው ክፍለ ዘመን

የ19ኛው ክ.ዘ መጀመሪያ ዓመታት ላይ የአካባቢ መሳፍንቶች ፖለቲካዊና አስተዳደራዊ ሁኔታውን ተቆጣጥረው የነበሩበትና ይህም ከዞኑ ጋር በተያያዘ በታሪክ የሚታወቁት እነ ታላቁ ራስ ዓሊ፣ታላቁ ራ ስ ጉግሳ የመሳሰ ሉት የሀይል ሚዛናቸው ጎላ ብሎ የሚታወቁት መቀመጫቸው ደብረታቦር ከተማ ነበር ።ይህ ዘመነ መሳፍንት በመባል የሚታወቀው ታሪካዊ ሁኔታ በዐጼ ቴውድሮስ አማካኝነት መለወጥ የቻ ለ ነው።

ዐጼ ቴውድሮስ የነበሯቸውን ዓላማዎች ዕውን ለማድረግ ካካሄዷቸው ታሪካ ዊ ክንዋኔዎች ውስጥ በዞናችን በተለይም ከደብረታቦር ጋፋት ጋር በቅርብ የተቆራኘ ሆኖ እ ናገኘዋለን።ዐጼ ቴውድሮስ ወ ታደራዊ፣ፖለቲካዊና ዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮቻቸውን አቅጣጫ የሚያሲዙበት መፍትሄ የሚሰጡበት መ ነሻና መደምደሚያቸው የአሁኗ የዞኑ ርዕሰ ከተማ ደብረታቦር ነበረች።

በ19ኛው ክ.ዘ ከዐጼ ቴውድሮስ በኋላ ስልጣን ላይ የወጡት ዐጼ ይኋንስ በያ ኔዋ ቤጌምድር በደብረ ታቦር አቅራቢያ ጋፋት አጠገብ ሰመርነሃ በተባለው ስፍራ ቤተመንግስታቸውን አሰርተው መቀመጫቸ ውን በማድረግ መላ አገሪቷን ለማስተዳደር ተጠቅመውባታል።ዐጼ ይኋንስ ከእሳቸው ቀድመው እንደነ በሩትና በቴክኖሎጂው ዘርፍ የታሪክና የባህል አሻራቸውን ትተው እንዳለፉት እሳቸውም ሀይማኖታዊ ተቋማትን በመገንባት ለግን ባታ ባህሉ ዕድ ገት አስተዋጽኦ አድርገዋል።

 

 

Select Language

English (United Kingdom)

Write Key Word

Comment

Your feed Back

Visitors Counter

mod_vvisit_countermod_vvisit_countermod_vvisit_countermod_vvisit_countermod_vvisit_countermod_vvisit_counter
mod_vvisit_counterToday3
mod_vvisit_counterYesterday3
mod_vvisit_counterThis week9
mod_vvisit_counterLast week20
mod_vvisit_counterThis month73
mod_vvisit_counterLast month71
mod_vvisit_counterAll days16557
Visitors Counter

Online guests

We have 1 guest onlinedeveloped by Tessema Mekrie

copy right @ south Gondar Administration